Testo Nat Baro

Testo Nat Baro

ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ
አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ
ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ
ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ
ናት ባሮ የወንዙ ዳር ኗሪ
አጊጣ ባልቦ መሳይ ድሪ
ሁሌ ላያት እንዳዲስ ገራሚ
ናት የባሮ የወንዙ ዳር ሎሚ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ጥቁሯ ወርቅ ቀጥ እንደ ሸምበቆ
አኳኋኗ በአታሞ ምት ረቆ
ፍቅር ሲሞቅ እሳት ነዶ ማታ
ውበት አየሁ ዳንኪራ ሲመታ
ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ
ናት የባሮ
ቶም ሰርታ በዣንጥላው ብረት
በጨረቃ ፍቅርን ያዜምንበት
የታንኳው ላይ የወንዙ ሽርሽር
እረፍት አጣው ትዝ ባለኝ ቁጥር
ያበቀላት የወንዙ ዳር ኑሮ
ናት የባሮ
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
መሸት ሲል ጀምበር አዘቅዝቆ
ቀዩን ሰማይ ውሃው አንፀባርቆ
እያየኋት በጨረቃ መብራት
አማረኝ የታንኳ ላይ እራት
ጉድ አረገኝ በውበት ሳር አስሮ
አዬ ባሮ
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ይሄ ልቤ የሆነብኝ ምነው
ሀሳቤ ሁሌ ከአዊሊ ነው
ልያት እንጂ ወይ ሄጄ ዳግመኛ
ባደርጋት የሁሌ ጓደኛ
ዓሳ ሆኖ ልኮኝ እንጀራዬ
ከአዲስ አበባው የትውልድ አምባዬ
ተመለስኩኝ በፍቅሯ ተይዤ
የሸገር ልጅ ባዶ ቅርጫት ይዤ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አገነ ገቲያ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አነ ሚየጎ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አጀሎዬ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ናት ባሮ አሳ አጠምድ ብሎ
ናት ባሮ ዘርግቶት መረቡን
ናት ባሮ እንዴት ለቆንጆ ሴት
ናት ባሮ ሰው ይጥላል ልቡን
ናት ባሮ ዓይኔ እሷ ላይ ቀርቶ
ናት ባሮ ዓሳ አጣሁ ለእራቴ
ናት ባሮ ባዶ ቅርጫት ይዤ
ናት ባሮ ተመለስኩኝ ቤቴ
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዙሪያ ሴት
የገዛችው የልቤን ውስጥ ስሜት
ናት ባሮ ናት ባሮ የወንዙ ዳር ቆንጆ
የሰራችው በልቤ ላይ ጎጆ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አገነ ገቲያ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አነ ሚየጎ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አጀሎዬ
ኚላል ባድ ኦፔኖ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አገነ ገቲያ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አነ ሚየጎ
ኚላል ባድ ኦፔኖ አጀሎዬ
Testi Teddy Afro